ዘዳግም 33:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 እሱ ሕዝቡን ይወዳል፤+ቅዱስ የሆነው ሕዝብ ሁሉ እጅህ ውስጥ ነው።+ እነሱም እግርህ ሥር ተቀምጠዋል፤+ቃልህንም ይሰማሉ።+ 1 ሳሙኤል 2:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 እሱ የታማኞቹን እርምጃ ይጠብቃል፤+ክፉዎች ግን በጨለማ ውስጥ ጸጥ እንዲሉ ይደረጋሉ፤+ሰው የበላይ የሚሆነው በኃይሉ አይደለምና።+ መዝሙር 37:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 መንገድህን ለይሖዋ አደራ ስጥ፤*+በእሱ ታመን፤ እሱም ለአንተ ሲል እርምጃ ይወስዳል።+