14 ለይሖዋ በእሳት የሚቃጠል መባ አድርጎ የሚያቀርበውም እነዚህን ነው፦ አንጀቱን የሸፈነውን ስብ፣ በአንጀቱ ዙሪያ ያለውን ስብ በሙሉ፣+ 15 ሁለቱን ኩላሊቶችና በእነሱ ላይ ማለትም በሽንጡ አካባቢ ያለውን ስብ ያቀርባል። በጉበቱ ላይ ያለውንም ሞራ ከኩላሊቶቹ ጋር አብሮ ያነሳል። 16 ካህኑም እንደ ምግብ ይኸውም ደስ የሚያሰኝ መዓዛ እንዳለው በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጨሳቸዋል። ስቡ ሁሉ የይሖዋ ነው።+