አስቴር 8:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 የንጉሡ ድንጋጌና ሕግ በተሰማባቸው በሁሉም አውራጃዎችና ከተሞች የሚኖሩ አይሁዳውያን ተደሰቱ፤ ሐሴትም አደረጉ፤ የግብዣና የፈንጠዝያ ቀን ሆነ። ብዙዎቹ የምድሪቱ ነዋሪዎች አይሁዳውያንን ከመፍራታቸው የተነሳ አይሁዳዊ ሆኑ።+ ኢሳይያስ 14:1, 2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ይሖዋ ለያዕቆብ ምሕረት ያሳያልና፤+ እስራኤልንም እንደገና ይመርጠዋል።+ በምድራቸው ላይ ያሰፍራቸዋል፤*+ የባዕድ አገር ሰዎችም ከእነሱ ጋር ይሆናሉ፤ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይጣበቃሉ።+ 2 ሕዝቦችም ይወስዷቸዋል፤ ወደ ገዛ ስፍራቸውም ይመልሷቸዋል፤ የእስራኤልም ቤት በይሖዋ ምድር ላይ ወንድና ሴት አገልጋዮቻቸው ያደርጓቸዋል፤+ ማርከው የወሰዷቸውንም ይማርካሉ፤ አስገድደው ያሠሯቸው የነበሩትንም* ይገዟቸዋል። ኢሳይያስ 49:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 ነገሥታት ይንከባከቡሻል፤+ልዕልቶቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ። በግንባራቸው ተደፍተው ይሰግዱልሻል፤+የእግርሽንም አቧራ ይልሳሉ፤+አንቺም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቂያለሽ፤እኔን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩም።”+ ኢሳይያስ 60:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 የጨቋኞችሽ ወንዶች ልጆች መጥተው በፊትሽ ይሰግዳሉ፤የሚያዋርዱሽ ሁሉ እግርሽ ሥር ይደፋሉ፤ደግሞም የይሖዋ ከተማ፣የእስራኤልም ቅዱስ አምላክ ንብረት የሆንሽ ጽዮን ብለው ይጠሩሻል።+ ኢሳይያስ 61:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 “እንግዳ ሰዎች መጥተው መንጎቻችሁን ይጠብቃሉ፤የባዕድ አገር ሰዎችም+ ገበሬዎቻችሁና የወይን አትክልት ሠራተኞቻችሁ ይሆናሉ።+
17 የንጉሡ ድንጋጌና ሕግ በተሰማባቸው በሁሉም አውራጃዎችና ከተሞች የሚኖሩ አይሁዳውያን ተደሰቱ፤ ሐሴትም አደረጉ፤ የግብዣና የፈንጠዝያ ቀን ሆነ። ብዙዎቹ የምድሪቱ ነዋሪዎች አይሁዳውያንን ከመፍራታቸው የተነሳ አይሁዳዊ ሆኑ።+
14 ይሖዋ ለያዕቆብ ምሕረት ያሳያልና፤+ እስራኤልንም እንደገና ይመርጠዋል።+ በምድራቸው ላይ ያሰፍራቸዋል፤*+ የባዕድ አገር ሰዎችም ከእነሱ ጋር ይሆናሉ፤ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይጣበቃሉ።+ 2 ሕዝቦችም ይወስዷቸዋል፤ ወደ ገዛ ስፍራቸውም ይመልሷቸዋል፤ የእስራኤልም ቤት በይሖዋ ምድር ላይ ወንድና ሴት አገልጋዮቻቸው ያደርጓቸዋል፤+ ማርከው የወሰዷቸውንም ይማርካሉ፤ አስገድደው ያሠሯቸው የነበሩትንም* ይገዟቸዋል።
23 ነገሥታት ይንከባከቡሻል፤+ልዕልቶቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ። በግንባራቸው ተደፍተው ይሰግዱልሻል፤+የእግርሽንም አቧራ ይልሳሉ፤+አንቺም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቂያለሽ፤እኔን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩም።”+
14 የጨቋኞችሽ ወንዶች ልጆች መጥተው በፊትሽ ይሰግዳሉ፤የሚያዋርዱሽ ሁሉ እግርሽ ሥር ይደፋሉ፤ደግሞም የይሖዋ ከተማ፣የእስራኤልም ቅዱስ አምላክ ንብረት የሆንሽ ጽዮን ብለው ይጠሩሻል።+