-
2 ነገሥት 25:4-7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 የከተማዋ ቅጥር ተደረመሰ፤+ ከለዳውያን ከተማዋን ከበው ሳለም ወታደሮቹ ሁሉ በንጉሡ የአትክልት ቦታ አቅራቢያ ባለው መንገድ፣ በሁለቱ ቅጥሮች መካከል በሚገኘው በር በኩል በሌሊት ወጥተው ሸሹ፤ ንጉሡም ወደ አረባ በሚወስደው መንገድ ሄደ።+ 5 ይሁንና የከለዳውያን ሠራዊት ንጉሡን አሳደደ፤ እሱንም በኢያሪኮ በረሃማ ሜዳ ላይ ደረሱበት፤ ወታደሮቹም ሁሉ ጥለውት ተበታተኑ። 6 ከዚያም ንጉሡን ይዘው+ በሪብላ ወደነበረው የባቢሎን ንጉሥ አመጡት፤ ደግሞም ፈረዱበት። 7 የሴዴቅያስን ወንዶች ልጆች ዓይኑ እያየ አረዷቸው፤ ከዚያም ናቡከደነጾር የሴዴቅያስን ዓይን አሳወረ፤ በመዳብ የእግር ብረት አስሮም ወደ ባቢሎን ወሰደው።+
-
-
ኤርምያስ 52:7-11አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
7 በመጨረሻም የከተማዋ ቅጥር ተነደለ፤ ከለዳውያን ከተማዋን ከበው ሳለም ወታደሮቹ ሁሉ በንጉሡ የአትክልት ቦታ አቅራቢያ ባለው መንገድ፣ በሁለቱ ቅጥሮች መካከል በሚገኘው በር በኩል በሌሊት ከከተማዋ ወጥተው ሸሹ፤ ወደ አረባ የሚወስደውንም አቅጣጫ ይዘው ሄዱ።+ 8 ይሁንና የከለዳውያን ሠራዊት ንጉሡን አሳደደ፤ ሴዴቅያስንም+ በኢያሪኮ በረሃማ ሜዳ ላይ ደረሱበት፤ ወታደሮቹም ሁሉ ጥለውት ተበታተኑ። 9 ከዚያም ንጉሡን ይዘው በሃማት ምድር በምትገኘው በሪብላ ወደነበረው የባቢሎን ንጉሥ አመጡት፤ እሱም ፈረደበት። 10 የባቢሎንም ንጉሥ የሴዴቅያስን ወንዶች ልጆች ዓይኑ እያየ አረዳቸው፤ በተጨማሪም የይሁዳን መኳንንት ሁሉ በዚያው በሪብላ አረዳቸው። 11 ከዚያም የባቢሎን ንጉሥ፣ የሴዴቅያስን ዓይን አሳወረ፤+ በመዳብ የእግር ብረት አስሮ ወደ ባቢሎን ወሰደው፤ እስከ ዕለተ ሞቱም ድረስ በእስር ቤት አቆየው።
-