2 “‘አንድ ሰው ለይሖዋ የእህል መባ+ የሚያቀርብ ከሆነ መባው የላመ ዱቄት መሆን አለበት፤ በላዩም ላይ ዘይት ያፍስበት፤ ነጭ ዕጣንም ያስቀምጥበት።+ 2 ከዚያም ካህናት ወደሆኑት የአሮን ወንዶች ልጆች ያመጣዋል፤ ካህኑም ከላዩ ላይ አንድ እፍኝ የላመ ዱቄትና ዘይት፣ ነጭ ዕጣኑንም በሙሉ ይወስዳል፤ ይህንም አምላክ መላውን መባ እንዲያስበው የሚያደርግ መባ+ ይኸውም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጨሰዋል።