2 ነገሥት 24:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን ከእናቱ፣ ከአገልጋዮቹ፣ ከመኳንንቱና ከቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱ+ ጋር ሆኖ ወደ ባቢሎን ንጉሥ+ ወጣ፤ የባቢሎንም ንጉሥ በነገሠ በስምንተኛው ዓመት ዮአኪንን ማርኮ ወሰደው።+ 2 ነገሥት 24:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 በዚህ መንገድ ዮአኪንን+ ወደ ባቢሎን በግዞት ወሰደው፤+ በተጨማሪም የንጉሡን እናት፣ የንጉሡን ሚስቶች፣ የቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱንና በምድሪቱ ውስጥ ያሉትን ታላላቅ ሰዎች ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን በግዞት ወሰደ። 2 ዜና መዋዕል 36:9, 10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ዮአኪን+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 18 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለሦስት ወር ከአሥር ቀን ገዛ፤ እሱም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ።+ 10 በዓመቱ መጀመሪያ* ላይ ንጉሥ ናቡከደነጾር አገልጋዮቹን ልኮ በይሖዋ ቤት ካሉት ውድ ዕቃዎች+ ጋር ወደ ባቢሎን አመጣው።+ የአባቱን ወንድም ሴዴቅያስንም በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠው።+ ኤርምያስ 24:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 ከዚያም ይሖዋ በለስ የያዙ ሁለት ቅርጫቶችን በይሖዋ ቤተ መቅደስ ፊት ለፊት ተቀምጠው አሳየኝ፤ ይህም የሆነው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* የይሁዳን ንጉሥ የኢዮዓቄምን ልጅ+ ኢኮንያንን፣*+ ከይሁዳ መኳንንት፣ ከእጅ ጥበብ ባለሙያዎቹና ከአንጥረኞቹ* ጋር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን በግዞት ከወሰዳቸው በኋላ ነው።+ ኤርምያስ 29:1, 2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 ነቢዩ ኤርምያስ፣ በግዞት ከተወሰዱት ሰዎች መካከል በሕይወት ለቀሩት ሽማግሌዎች፣ ለካህናቱ፣ ለነቢያቱና ናቡከደነጾር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን በግዞት ለወሰደው ሕዝብ ሁሉ ከኢየሩሳሌም የላከው ደብዳቤ ቃል ይህ ነው፦ 2 ይህም የሆነው ንጉሥ ኢኮንያን፣+ የንጉሡ እናት፣*+ ባለሥልጣናቱ፣ የይሁዳና የኢየሩሳሌም መኳንንት፣ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎቹና አንጥረኞቹ* ከኢየሩሳሌም ከሄዱ በኋላ ነው።+
12 የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን ከእናቱ፣ ከአገልጋዮቹ፣ ከመኳንንቱና ከቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱ+ ጋር ሆኖ ወደ ባቢሎን ንጉሥ+ ወጣ፤ የባቢሎንም ንጉሥ በነገሠ በስምንተኛው ዓመት ዮአኪንን ማርኮ ወሰደው።+
15 በዚህ መንገድ ዮአኪንን+ ወደ ባቢሎን በግዞት ወሰደው፤+ በተጨማሪም የንጉሡን እናት፣ የንጉሡን ሚስቶች፣ የቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱንና በምድሪቱ ውስጥ ያሉትን ታላላቅ ሰዎች ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን በግዞት ወሰደ።
9 ዮአኪን+ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 18 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ለሦስት ወር ከአሥር ቀን ገዛ፤ እሱም በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር አደረገ።+ 10 በዓመቱ መጀመሪያ* ላይ ንጉሥ ናቡከደነጾር አገልጋዮቹን ልኮ በይሖዋ ቤት ካሉት ውድ ዕቃዎች+ ጋር ወደ ባቢሎን አመጣው።+ የአባቱን ወንድም ሴዴቅያስንም በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠው።+
24 ከዚያም ይሖዋ በለስ የያዙ ሁለት ቅርጫቶችን በይሖዋ ቤተ መቅደስ ፊት ለፊት ተቀምጠው አሳየኝ፤ ይህም የሆነው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* የይሁዳን ንጉሥ የኢዮዓቄምን ልጅ+ ኢኮንያንን፣*+ ከይሁዳ መኳንንት፣ ከእጅ ጥበብ ባለሙያዎቹና ከአንጥረኞቹ* ጋር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን በግዞት ከወሰዳቸው በኋላ ነው።+
29 ነቢዩ ኤርምያስ፣ በግዞት ከተወሰዱት ሰዎች መካከል በሕይወት ለቀሩት ሽማግሌዎች፣ ለካህናቱ፣ ለነቢያቱና ናቡከደነጾር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን በግዞት ለወሰደው ሕዝብ ሁሉ ከኢየሩሳሌም የላከው ደብዳቤ ቃል ይህ ነው፦ 2 ይህም የሆነው ንጉሥ ኢኮንያን፣+ የንጉሡ እናት፣*+ ባለሥልጣናቱ፣ የይሁዳና የኢየሩሳሌም መኳንንት፣ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎቹና አንጥረኞቹ* ከኢየሩሳሌም ከሄዱ በኋላ ነው።+