-
ዕብራውያን 8:8-12አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
8 አምላክ በሕዝቡ ላይ ጉድለት ስላገኘ እንዲህ ብሎ ተናግሯልና፦ “‘እነሆ፣ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ።* 9 ‘ይህም ቃል ኪዳን አባቶቻቸውን እጃቸውን ይዤ ከግብፅ ምድር እየመራሁ ባወጣኋቸው ቀን+ ከእነሱ ጋር እንደገባሁት ዓይነት ቃል ኪዳን አይሆንም፤ ምክንያቱም እነሱ በቃል ኪዳኔ አልጸኑም፤ በመሆኑም ችላ አልኳቸው’ ይላል ይሖዋ።*
10 “‘ከዚያ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና’ ይላል ይሖዋ።* ‘ሕግጋቴን በአእምሯቸው ውስጥ አኖራለሁ፤ በልባቸውም ላይ እጽፋቸዋለሁ።+ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።+
11 “‘እነሱም እያንዳንዳቸው የአገራቸውን ሰው፣ እያንዳንዳቸውም ወንድማቸውን “ይሖዋን* እወቅ!” ብለው ከእንግዲህ አያስተምሩም። ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ ሁሉም ያውቁኛልና። 12 ለክፉ ሥራቸው ምሕረት አደርግላቸዋለሁና፤ ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስታውስም።’”+
-