ዘሌዋውያን 26:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ዝናብን በወቅቱ አዘንብላችኋለሁ፤+ ምድሪቱም ምርቷን ትሰጣለች፤+ የሜዳ ዛፎችም ፍሬያቸውን ይሰጣሉ። መዝሙር 85:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 አዎ፣ ይሖዋ መልካም ነገር* ይሰጣል፤+ምድራችንም ምርቷን ትሰጣለች።+ ኢሳይያስ 35:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 በእርግጥ ያብባል፤+ሐሴት ያደርጋል፤ በደስታም እልል ይላል። የሊባኖስ ክብር ይሰጠዋል፤+የቀርሜሎስንና+ የሳሮንን+ ግርማ ይለብሳል። የይሖዋን ክብር፣ የአምላካችንንም ግርማ ያያሉ። ሕዝቅኤል 36:30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 በረሃብ የተነሳ በብሔራት መካከል ዳግመኛ ውርደት እንዳይደርስባችሁ፣ የዛፉን ፍሬና የእርሻውን ምርት አበዛለሁ።+
2 በእርግጥ ያብባል፤+ሐሴት ያደርጋል፤ በደስታም እልል ይላል። የሊባኖስ ክብር ይሰጠዋል፤+የቀርሜሎስንና+ የሳሮንን+ ግርማ ይለብሳል። የይሖዋን ክብር፣ የአምላካችንንም ግርማ ያያሉ።