ኤርምያስ 49:17, 18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 “ኤዶምም አስፈሪ ቦታ ትሆናለች።+ በእሷ አጠገብ የሚያልፍ ሁሉ በፍርሃት አፍጥጦ ይመለከታል፤ በደረሱባት መቅሰፍቶች ሁሉ የተነሳም ያፏጫል። 18 ሰዶምና ገሞራ እንዲሁም በአካባቢያቸው ያሉት ከተሞች በተደመሰሱ ጊዜ እንደሆነው ሁሉ”+ ይላል ይሖዋ፤ “በዚያ ማንም አይኖርም፤ አንድም ሰው በዚያ አይቀመጥም።+ ሕዝቅኤል 25:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እጄን በኤዶምም ላይ እዘረጋለሁ፤ ከምድሪቱም ላይ ሰውንም ሆነ ከብትን አጠፋለሁ፤ ባድማም አደርጋታለሁ።+ ከቴማን አንስቶ እስከ ዴዳን ድረስ በሰይፍ ይወድቃሉ።+ ሚልክያስ 1:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 “ኤዶም* ‘ተደምስሰናል፤ ሆኖም ተመልሰን የፈራረሱትን ዳግመኛ እንገነባለን’ ቢልም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሱ ይገነባሉ፤ እኔ ግን አፈርሳለሁ፤ ቦታዎቹ “የክፋት ምድር፣” እነሱ ደግሞ “ይሖዋ ለዘላለም ያወገዘው ሕዝብ” ተብለው ይጠራሉ።+
17 “ኤዶምም አስፈሪ ቦታ ትሆናለች።+ በእሷ አጠገብ የሚያልፍ ሁሉ በፍርሃት አፍጥጦ ይመለከታል፤ በደረሱባት መቅሰፍቶች ሁሉ የተነሳም ያፏጫል። 18 ሰዶምና ገሞራ እንዲሁም በአካባቢያቸው ያሉት ከተሞች በተደመሰሱ ጊዜ እንደሆነው ሁሉ”+ ይላል ይሖዋ፤ “በዚያ ማንም አይኖርም፤ አንድም ሰው በዚያ አይቀመጥም።+
13 ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እጄን በኤዶምም ላይ እዘረጋለሁ፤ ከምድሪቱም ላይ ሰውንም ሆነ ከብትን አጠፋለሁ፤ ባድማም አደርጋታለሁ።+ ከቴማን አንስቶ እስከ ዴዳን ድረስ በሰይፍ ይወድቃሉ።+
4 “ኤዶም* ‘ተደምስሰናል፤ ሆኖም ተመልሰን የፈራረሱትን ዳግመኛ እንገነባለን’ ቢልም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሱ ይገነባሉ፤ እኔ ግን አፈርሳለሁ፤ ቦታዎቹ “የክፋት ምድር፣” እነሱ ደግሞ “ይሖዋ ለዘላለም ያወገዘው ሕዝብ” ተብለው ይጠራሉ።+