15 በዚህ መንገድ ዮአኪንን+ ወደ ባቢሎን በግዞት ወሰደው፤+ በተጨማሪም የንጉሡን እናት፣ የንጉሡን ሚስቶች፣ የቤተ መንግሥት ባለሥልጣናቱንና በምድሪቱ ውስጥ ያሉትን ታላላቅ ሰዎች ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን በግዞት ወሰደ። 16 ደግሞም የባቢሎን ንጉሥ ኃያላን የሆኑና ለጦርነት የሠለጠኑ ወንዶችን በሙሉ ይኸውም 7,000 ተዋጊዎችን እንዲሁም 1,000 የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችንና አንጥረኞችን ወደ ባቢሎን በግዞት ወሰደ።