11 ሙሴም አምላኩን ይሖዋን ተማጸነ፤+ እንዲህም አለ፦ “ይሖዋ ሆይ፣ በታላቅ ኃይልና በብርቱ እጅ ከግብፅ ምድር ካወጣሃቸው በኋላ በሕዝብህ ላይ ቁጣህ የሚነደው ለምንድን ነው?+ 12 ግብፃውያንስ ‘ቀድሞውንም ቢሆን መርቶ ያወጣቸው ተንኮል አስቦ ነው። በተራሮች ላይ ሊገድላቸውና ከምድር ገጽ ሊያጠፋቸው ፈልጎ ነው’ ለምን ይበሉ?+ ከሚነደው ቁጣህ ተመለስ፤ በሕዝብህ ላይ ይህን ጥፋት ለማምጣት ያደረግከውን ውሳኔ እስቲ እንደገና አስበው።