የሐዋርያት ሥራ 2:40 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 40 በሌላ ብዙ ቃልም በሚገባ* መሠከረላቸው፤ “ከዚህ ጠማማ ትውልድ ዳኑ” እያለም አጥብቆ አሳሰባቸው።+ 1 ጢሞቴዎስ 4:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ለራስህና ለምታስተምረው ትምህርት ምንጊዜም ትኩረት ስጥ።+ በእነዚህ ነገሮች ጽና፤ ይህን በማድረግ ራስህንም ሆነ የሚሰሙህን ታድናለህና።+