16 “በይሖዋ ስም የነገርከንን ቃል አንሰማም። 17 ይልቁንም አፋችን የተናገረውን ቃል ሁሉ መፈጸማችን አይቀርም፤ እኛና አባቶቻችን እንዲሁም ነገሥታታችንና መኳንንታችን በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ እናደርግ እንደነበረው ‘ለሰማይ ንግሥት’ መሥዋዕት እናቀርባለን፤ ለእሷም የመጠጥ መባ እናፈሳለን፤+ በዚያን ጊዜ እስክንጠግብ ድረስ እንበላና ተመችቶን እንኖር ነበር፤ ጥፋት የሚባል ነገርም አልገጠመንም።