-
ዳንኤል 4:18አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
18 “‘እኔ ንጉሥ ናቡከደነጾር ያየሁት ሕልም ይህ ነው፤ አሁንም ብልጣሶር ሆይ፣ በመንግሥቴ ውስጥ የሚኖሩት ሌሎቹ ጠቢባን ሁሉ ትርጉሙን ሊያሳውቁኝ ስላልቻሉ አንተ ትርጉሙን ንገረኝ።+ የቅዱሳን አማልክት መንፈስ በውስጥህ ስላለ ትርጉሙን ልታሳውቀኝ ትችላለህ።’
-
-
ዳንኤል 5:11, 12አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
11 በመንግሥትህ ውስጥ የቅዱሳን አማልክት መንፈስ ያለበት ሰው* አለ። በአባትህ ዘመን እንደ አማልክት ጥበብ ያለ ጥበብ፣ የእውቀት ብርሃንና ጥልቅ ማስተዋል ተገኝቶበት ነበር።+ አባትህ ንጉሥ ናቡከደነጾር የአስማተኛ ካህናቱ፣ የጠንቋዮቹ፣ የከለዳውያኑና* የኮከብ ቆጣሪዎቹ አለቃ አድርጎ ሾመው፤+ ንጉሥ ሆይ፣ ይህን ያደረገው አባትህ ነው። 12 ንጉሡ፣ ብልጣሶር ብሎ የሰየመው ዳንኤል+ ሕልምን በመተርጎም ረገድ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ችሎታ፣ እውቀትና ጥልቅ ማስተዋል እንዲሁም እንቆቅልሽንና የተወሳሰቡ ችግሮችን የመፍታት* ችሎታ ነበረው።+ እንግዲህ ዳንኤል ይጠራ፤ እሱም ትርጉሙን ይነግርሃል።”
-