4 በዚህ ጊዜ የተገደለችው ሴት ባል የሆነው ሌዋዊ+ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔና ቁባቴ የቢንያም በሆነችው በጊብዓ ለማደር ወደዚያ መጥተን ነበር።+ 5 የጊብዓ ነዋሪዎችም በእኔ ላይ ተነሱብኝ፤ በሌሊት መጥተውም ቤቱን ከበቡ። ለመግደል ያሰቡት እኔን ነበር፤ ሆኖም ቁባቴን ደፈሯት፤ እሷም ሞተች።+ 6 እኔም የቁባቴን አስከሬን ወስጄ ቆራረጥኩት፤ ከዚያም ወደ እያንዳንዱ የእስራኤል ርስት ላክሁት፤+ ምክንያቱም እነሱ በእስራኤል ውስጥ አሳፋሪና አስነዋሪ ድርጊት ፈጽመዋል።