ዘዳግም 6:10-12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 “አምላክህ ይሖዋ ለአንተ ለመስጠት ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደማለላቸው ምድር+ ሲያስገባህና በዚያም አንተ ያልገነባሃቸውን ታላላቅና ያማሩ ከተሞች፣+ 11 አንተ ባልደከምክባቸው የተለያዩ መልካም ነገሮች የተሞሉ ቤቶችን፣ አንተ ያልቦረቦርካቸውን የውኃ ማጠራቀሚያዎች እንዲሁም አንተ ያልተከልካቸውን የወይን ተክሎችና የወይራ ዛፎች ስታገኝ፣ በልተህም ስትጠግብ+ 12 ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን ይሖዋን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ።+ ዘዳግም 8:12-14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 በልተህ ስትጠግብ፣ ጥሩ ጥሩ ቤቶችን ሠርተህ በዚያ መኖር ስትጀምር፣+ 13 ከብትህና መንጋህ ሲበዛ፣ ብርህና ወርቅህ ሲበራከት እንዲሁም የአንተ የሆነው ሁሉ እየበዛ ሲሄድ 14 ልብህ እንዳይታበይና+ ከግብፅ ምድር ይኸውም ከባርነት ቤት ያወጣህን አምላክህን ይሖዋን እንዳያስረሳህ ተጠንቀቅ፤+ ዘዳግም 32:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 የሹሩን* ሲወፍር በዓመፀኝነት ተራገጠ። ሰባህ፤ ፈረጠምክ፤ ደለብክ።+ ስለሆነም የሠራውን አምላክ ተወ፤+አዳኝ የሆነለትን ዓለት ናቀ። ዘዳግም 32:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 አባት የሆነህን ዓለት ረሳኸው፤+የወለደህንም አምላክ አላስታወስክም።+ ኢሳይያስ 17:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 አንቺ፣* አዳኝ አምላክሽን ረስተሻልና፤+መሸሸጊያ ዓለትሽንም+ አላስታወስሽም። ያማሩ ተክሎችን ያለማሽውናበመካከሉም የባዕድ* ቡቃያ የተከልሽው ለዚህ ነው።
10 “አምላክህ ይሖዋ ለአንተ ለመስጠት ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደማለላቸው ምድር+ ሲያስገባህና በዚያም አንተ ያልገነባሃቸውን ታላላቅና ያማሩ ከተሞች፣+ 11 አንተ ባልደከምክባቸው የተለያዩ መልካም ነገሮች የተሞሉ ቤቶችን፣ አንተ ያልቦረቦርካቸውን የውኃ ማጠራቀሚያዎች እንዲሁም አንተ ያልተከልካቸውን የወይን ተክሎችና የወይራ ዛፎች ስታገኝ፣ በልተህም ስትጠግብ+ 12 ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን ይሖዋን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ።+
12 በልተህ ስትጠግብ፣ ጥሩ ጥሩ ቤቶችን ሠርተህ በዚያ መኖር ስትጀምር፣+ 13 ከብትህና መንጋህ ሲበዛ፣ ብርህና ወርቅህ ሲበራከት እንዲሁም የአንተ የሆነው ሁሉ እየበዛ ሲሄድ 14 ልብህ እንዳይታበይና+ ከግብፅ ምድር ይኸውም ከባርነት ቤት ያወጣህን አምላክህን ይሖዋን እንዳያስረሳህ ተጠንቀቅ፤+