ኢሳይያስ 54:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ልጆችሽም* ሁሉ ከይሖዋ የተማሩ ይሆናሉ፤+የልጆችሽም* ሰላም ብዙ ይሆናል።+ ኤርምያስ 24:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 እኔ ይሖዋ መሆኔን እንዲያውቁም ልብ እሰጣቸዋለሁ።+ በሙሉ ልባቸው ወደ እኔ ስለሚመለሱ+ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።+ ኤርምያስ 31:34 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 “እነሱም እያንዳንዳቸው ባልንጀራቸውን፣ እያንዳንዳቸውም ወንድማቸውን ‘ይሖዋን እወቅ!’ ብለው ከእንግዲህ አያስተምሩም፤+ ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ ሁሉም ያውቁኛልና”+ ይላል ይሖዋ። “በደላቸውን ይቅር እላለሁና፤ ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ አላስታውስም።”+
34 “እነሱም እያንዳንዳቸው ባልንጀራቸውን፣ እያንዳንዳቸውም ወንድማቸውን ‘ይሖዋን እወቅ!’ ብለው ከእንግዲህ አያስተምሩም፤+ ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ ሁሉም ያውቁኛልና”+ ይላል ይሖዋ። “በደላቸውን ይቅር እላለሁና፤ ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ አላስታውስም።”+