21 “‘ክፉ ሰው ከሠራው ኃጢአት ሁሉ ቢመለስ፣ ያወጣኋቸውን ደንቦች ቢጠብቅ እንዲሁም ፍትሐዊና ጽድቅ የሆነ ነገር ቢያደርግ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል። ፈጽሞ አይሞትም።+ 22 ከሠራው በደል ውስጥ አንዱም አይታሰብበትም።+ በሠራው ጽድቅ የተነሳ በሕይወት ይኖራል።’+
23 “‘እኔ በክፉ ሰው ሞት ደስ እሰኛለሁ?’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። ‘እኔ ደስ የምሰኘው ከመንገዱ ቢመለስና በሕይወት ቢኖር አይደለም?’+