2 በዘመኑ መጨረሻ
የይሖዋ ቤት ተራራ
ከተራሮች አናት በላይ ጸንቶ ይቆማል፤+
ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤
ብሔራትም ሁሉ ወደዚያ ይጎርፋሉ።+
3 ብዙ ሕዝቦችም ሄደው እንዲህ ይላሉ፦
“ኑ፤ ወደ ይሖዋ ተራራ፣
ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ።+
እሱ ስለ መንገዶቹ ያስተምረናል፤
በጎዳናዎቹም እንሄዳለን።”+
ሕግ ከጽዮን፣
የይሖዋም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።+
4 እሱ በብሔራት መካከል ይፈርዳል፤
ከብዙ ሕዝቦች ጋር በተያያዘም ሁሉንም ነገር ያቀናል።
እነሱ ሰይፋቸውን ማረሻ፣
ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ።+
አንዱ ብሔር በሌላው ብሔር ላይ ሰይፍ አያነሳም፤
ከእንግዲህ ወዲህ ጦርነት አይማሩም።+