ዘፍጥረት 49:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ሴሎ* እስኪመጣ ድረስ በትረ መንግሥት ከይሁዳ፣+ የአዛዥም በትር ከእግሮቹ መካከል አይወጣም፤+ ለእሱም ሕዝቦች ይታዘዙለታል።+ 1 ዜና መዋዕል 5:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ይሁዳ+ ከወንድሞቹ የሚበልጥ ከመሆኑም ሌላ መሪ+ የሚሆነው የተገኘው ከእሱ ነው፤ ሆኖም የብኩርና መብቱን ያገኘው ዮሴፍ ነበር። ኢሳይያስ 9:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ልጅ ተወልዶልናልና፤+ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል፤ገዢነትም* በጫንቃው ላይ ይሆናል።+ ስሙ ድንቅ መካሪ፣+ ኃያል አምላክ፣+ የዘላለም አባትና የሰላም መስፍን ይባላል። ማቴዎስ 2:4-6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ንጉሡም የሕዝቡን የካህናት አለቆችና ጸሐፍት በሙሉ ሰብስቦ ክርስቶስ* የት እንደሚወለድ ጠየቃቸው። 5 እነሱም እንዲህ አሉት፦ “በይሁዳ በምትገኘው በቤተልሔም+ ነው፤ ምክንያቱም ነቢዩ እንዲህ ብሎ ጽፏል፦ 6 ‘በይሁዳ ምድር የምትገኚው አንቺ ቤተልሔም ሆይ፣ ለሕዝቤ ለእስራኤል እረኛ የሚሆን ገዢ ከአንቺ ስለሚወጣ በይሁዳ ገዢዎች ዘንድ ከሁሉ የተናቅሽ ከተማ አትሆኚም።’”+ ሉቃስ 1:32, 33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 እሱም ታላቅ ይሆናል፤+ የልዑሉም አምላክ ልጅ ይባላል፤+ ይሖዋ* አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤+ 33 በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘላለም ንጉሥ ሆኖ ይገዛል፤ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም።”+ ሉቃስ 2:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 በዛሬው ዕለት በዳዊት ከተማ+ አዳኝ+ ተወልዶላችኋልና፤ እሱም ጌታ ክርስቶስ ነው።+ ዮሐንስ 7:42 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 42 ቅዱስ መጽሐፉ ክርስቶስ ከዳዊት ዘርና+ ዳዊት ከኖረበት መንደር+ ከቤተልሔም+ እንደሚመጣ ይናገር የለም?”
6 ልጅ ተወልዶልናልና፤+ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል፤ገዢነትም* በጫንቃው ላይ ይሆናል።+ ስሙ ድንቅ መካሪ፣+ ኃያል አምላክ፣+ የዘላለም አባትና የሰላም መስፍን ይባላል።
4 ንጉሡም የሕዝቡን የካህናት አለቆችና ጸሐፍት በሙሉ ሰብስቦ ክርስቶስ* የት እንደሚወለድ ጠየቃቸው። 5 እነሱም እንዲህ አሉት፦ “በይሁዳ በምትገኘው በቤተልሔም+ ነው፤ ምክንያቱም ነቢዩ እንዲህ ብሎ ጽፏል፦ 6 ‘በይሁዳ ምድር የምትገኚው አንቺ ቤተልሔም ሆይ፣ ለሕዝቤ ለእስራኤል እረኛ የሚሆን ገዢ ከአንቺ ስለሚወጣ በይሁዳ ገዢዎች ዘንድ ከሁሉ የተናቅሽ ከተማ አትሆኚም።’”+
32 እሱም ታላቅ ይሆናል፤+ የልዑሉም አምላክ ልጅ ይባላል፤+ ይሖዋ* አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤+ 33 በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘላለም ንጉሥ ሆኖ ይገዛል፤ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም።”+