12 በአምስተኛው ወር፣ ከወሩም በአሥረኛው ቀን ይኸውም ንጉሥ ናቡከደነጾር በነገሠ በ19ኛው ዓመት፣ የዘቦች አለቃና የባቢሎን ንጉሥ አገልጋይ የሆነው ናቡዛራዳን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።+ 13 እሱም የይሖዋን ቤት፣ የንጉሡን ቤትና በኢየሩሳሌም የሚገኙ ቤቶችን በሙሉ አቃጠለ፤+ ትላልቅ ቤቶችንም ሁሉ በእሳት አጋየ። 14 ከዘቦቹ አለቃ ጋር የነበረው የከለዳውያን ሠራዊት በኢየሩሳሌም ዙሪያ ያለውን ቅጥር በሙሉ አፈረሰ።+