ማቴዎስ 10:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 የ12ቱ ሐዋርያት ስም የሚከተለው ነው፦+ በመጀመሪያ፣ ጴጥሮስ የተባለው ስምዖንና+ ወንድሙ እንድርያስ፣+ የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብና ወንድሙ ዮሐንስ፣+ ማቴዎስ 27:55, 56 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 55 ኢየሱስን ለማገልገል ከገሊላ ጀምሮ አብረውት የነበሩ ብዙ ሴቶችም+ እዚያ ሆነው ከሩቅ ይመለከቱ ነበር፤ 56 ከእነሱም መካከል መግደላዊቷ ማርያም፣ የያዕቆብና የዮሳ እናት ማርያም እንዲሁም የዘብዴዎስ ልጆች እናት ይገኙ ነበር።+ ማርቆስ 3:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብና የያዕቆብ ወንድም ዮሐንስ (እነዚህን ቦአኔርጌስ ብሎ የሰየማቸው ሲሆን ትርጉሙም “የነጎድጓድ ልጆች” ማለት ነው)፣+ ማርቆስ 10:35 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 35 ሁለቱ የዘብዴዎስ ልጆች+ ያዕቆብና ዮሐንስ ወደ እሱ ቀርበው “መምህር፣ የምንለምንህን ማንኛውንም ነገር እንድታደርግልን እንፈልጋለን” አሉት።+ ዮሐንስ 21:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ስምዖን ጴጥሮስ፣ ዲዲሞስ* የሚባለው ቶማስ፣+ የገሊላ ቃና ሰው የሆነው ናትናኤል፣+ የዘብዴዎስ ልጆችና+ ሌሎች ሁለት ደቀ መዛሙርቱ አብረው ነበሩ።
55 ኢየሱስን ለማገልገል ከገሊላ ጀምሮ አብረውት የነበሩ ብዙ ሴቶችም+ እዚያ ሆነው ከሩቅ ይመለከቱ ነበር፤ 56 ከእነሱም መካከል መግደላዊቷ ማርያም፣ የያዕቆብና የዮሳ እናት ማርያም እንዲሁም የዘብዴዎስ ልጆች እናት ይገኙ ነበር።+