ማቴዎስ 15:7-9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 እናንተ ግብዞች፣ ኢሳይያስ እንዲህ በማለት ስለ እናንተ በትክክል ተንብዮአል፦+ 8 ‘ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ እጅግ የራቀ ነው። 9 የሚያስተምሩት የሰውን ሥርዓት ስለሆነ እኔን የሚያመልኩት በከንቱ ነው።’”+ ማቴዎስ 23:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 “እናንተ ግብዞች ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! ከኮሰረት፣ ከእንስላልና ከከሙን አሥራት ትሰጣላችሁ፤+ ነገር ግን በሕጉ ውስጥ የሚገኙትን እንደ ፍትሕ፣+ ምሕረትና+ ታማኝነት ያሉ ይበልጥ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ችላ ትላላችሁ። እነዚያን ችላ ማለት ባይኖርባችሁም እነዚህን ነገሮች ማድረጋችሁ አስፈላጊ ነው።+ ሉቃስ 11:42 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 42 እናንተ ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! ምክንያቱም ከኮሰረት፣ ከጤና አዳምና ከሌሎች አትክልቶች ሁሉ አሥራት ትሰጣላችሁ፤+ ነገር ግን የአምላክን ፍትሕና እሱን መውደድን ችላ ትላላችሁ። እርግጥ አሥራት የመስጠት ግዴታ አለባችሁ፤ ሆኖም ሌሎቹን ነገሮች ችላ ማለት አልነበረባችሁም።+
7 እናንተ ግብዞች፣ ኢሳይያስ እንዲህ በማለት ስለ እናንተ በትክክል ተንብዮአል፦+ 8 ‘ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ እጅግ የራቀ ነው። 9 የሚያስተምሩት የሰውን ሥርዓት ስለሆነ እኔን የሚያመልኩት በከንቱ ነው።’”+
23 “እናንተ ግብዞች ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! ከኮሰረት፣ ከእንስላልና ከከሙን አሥራት ትሰጣላችሁ፤+ ነገር ግን በሕጉ ውስጥ የሚገኙትን እንደ ፍትሕ፣+ ምሕረትና+ ታማኝነት ያሉ ይበልጥ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ችላ ትላላችሁ። እነዚያን ችላ ማለት ባይኖርባችሁም እነዚህን ነገሮች ማድረጋችሁ አስፈላጊ ነው።+
42 እናንተ ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! ምክንያቱም ከኮሰረት፣ ከጤና አዳምና ከሌሎች አትክልቶች ሁሉ አሥራት ትሰጣላችሁ፤+ ነገር ግን የአምላክን ፍትሕና እሱን መውደድን ችላ ትላላችሁ። እርግጥ አሥራት የመስጠት ግዴታ አለባችሁ፤ ሆኖም ሌሎቹን ነገሮች ችላ ማለት አልነበረባችሁም።+