-
ሉቃስ 7:24-28አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
24 የዮሐንስ መልእክተኞች ከሄዱ በኋላ ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ እንዲህ ሲል ለሕዝቡ ይናገር ጀመር፦ “ወደ ምድረ በዳ የሄዳችሁት ምን ለማየት ነበር? ነፋስ የሚያወዛውዘውን ሸምበቆ?+ 25 ታዲያ ምን ለማየት ነበር የሄዳችሁት? ምርጥ ልብስ* የለበሰ ሰው ለማየት?+ የተንቆጠቆጠ ልብስ የሚለብሱና በቅንጦት የሚኖሩማ የሚገኙት በቤተ መንግሥት ነው። 26 ታዲያ ምን ለማየት ሄዳችሁ? ነቢይ? አዎ፣ እላችኋለሁ፣ ከነቢይም የሚበልጥ ነው።+ 27 ‘እነሆ፣ ከፊትህ እየሄደ መንገድህን እንዲያዘጋጅ መልእክተኛዬን ከአንተ አስቀድሜ እልካለሁ’ ተብሎ የተጻፈው ስለ እሱ ነው።+ 28 እላችኋለሁ፣ ከሴት ከተወለዱት መካከል ከዮሐንስ የሚበልጥ የለም፤ ሆኖም በአምላክ መንግሥት ዝቅተኛ የሆነው እንኳ ይበልጠዋል።”+
-