ሚልክያስ 2:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 እናንተም ‘ይህ የሆነው ለምንድን ነው?’ ብላችኋል። ይህ የሆነው ይሖዋ በአንተ ላይ ስለመሠከረብህ ነው፤ ምክንያቱም እሷ አጋርህና የቃል ኪዳን ሚስትህ* ሆና ሳለ በወጣትነት ሚስትህ ላይ ክህደት ፈጽመሃል።+ ማቴዎስ 5:32 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ በፆታ ብልግና* ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ ምንዝር ለመፈጸም እንድትጋለጥ ያደርጋታል፤ እንዲሁም በዚህ መንገድ የተፈታችን ሴት የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል።+ ማርቆስ 10:11, 12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ሚስቱን ፈቶ ሌላ የሚያገባ ሁሉ በማመንዘር+ ሚስቱን ይበድላል፤ 12 አንዲት ሴትም ብትሆን ባሏን ፈታ ሌላ ብታገባ ታመነዝራለች።”+ ሉቃስ 16:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 “ሚስቱን ፈቶ ሌላ የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል፤ ባሏ የፈታትንም ሴት የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል።+ ሮም 7:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 በመሆኑም ባሏ በሕይወት እያለ የሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ ትባላለች።+ ባሏ ከሞተ ግን ከእሱ ሕግ ነፃ ስለምትሆን የሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ አትባልም።+ 1 ቆሮንቶስ 7:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ላገቡት ሰዎች ይህን መመሪያ እሰጣለሁ፤ ይህ መመሪያ የጌታ እንጂ የእኔ አይደለም፤ ሚስት ከባሏ አትለያይ።+ ዕብራውያን 13:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ጋብቻ በሁሉ ዘንድ ክቡር፣ መኝታውም ከርኩሰት የጸዳ ይሁን፤+ አምላክ ሴሰኞችንና* አመንዝሮችን ይፈርድባቸዋልና።+
14 እናንተም ‘ይህ የሆነው ለምንድን ነው?’ ብላችኋል። ይህ የሆነው ይሖዋ በአንተ ላይ ስለመሠከረብህ ነው፤ ምክንያቱም እሷ አጋርህና የቃል ኪዳን ሚስትህ* ሆና ሳለ በወጣትነት ሚስትህ ላይ ክህደት ፈጽመሃል።+
32 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ በፆታ ብልግና* ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ ምንዝር ለመፈጸም እንድትጋለጥ ያደርጋታል፤ እንዲሁም በዚህ መንገድ የተፈታችን ሴት የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል።+
11 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ሚስቱን ፈቶ ሌላ የሚያገባ ሁሉ በማመንዘር+ ሚስቱን ይበድላል፤ 12 አንዲት ሴትም ብትሆን ባሏን ፈታ ሌላ ብታገባ ታመነዝራለች።”+
3 በመሆኑም ባሏ በሕይወት እያለ የሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ ትባላለች።+ ባሏ ከሞተ ግን ከእሱ ሕግ ነፃ ስለምትሆን የሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ አትባልም።+