ማቴዎስ 13:39 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 39 እንክርዳዱን የዘራው ጠላት፣ ዲያብሎስ ነው። መከሩ የዚህ ሥርዓት* መደምደሚያ ሲሆን አጫጆቹ ደግሞ መላእክት ናቸው። ማቴዎስ 28:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ያዘዝኳችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው።+ እነሆም እኔ እስከ ሥርዓቱ* መደምደሚያ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”+ ማርቆስ 13:3, 4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 በቤተ መቅደሱ ትይዩ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ሳለ ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ፣ ዮሐንስና እንድርያስ ብቻቸውን ሆነው እንዲህ በማለት ጠየቁት፦ 4 “እስቲ ንገረን፣ እነዚህ ነገሮች የሚፈጸሙት መቼ ነው? የእነዚህ ነገሮች ሁሉ መደምደሚያ መቅረቡን የሚያሳየው ምልክትስ ምንድን ነው?”+ ሉቃስ 21:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 እነሱም “መምህር፣ እነዚህ ነገሮች በእርግጥ የሚፈጸሙት መቼ ነው? እነዚህ ነገሮች የሚፈጸሙበትን ጊዜ የሚጠቁመው ምልክትስ ምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቁት።+
3 በቤተ መቅደሱ ትይዩ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ሳለ ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ፣ ዮሐንስና እንድርያስ ብቻቸውን ሆነው እንዲህ በማለት ጠየቁት፦ 4 “እስቲ ንገረን፣ እነዚህ ነገሮች የሚፈጸሙት መቼ ነው? የእነዚህ ነገሮች ሁሉ መደምደሚያ መቅረቡን የሚያሳየው ምልክትስ ምንድን ነው?”+