30 ከእነሱ ራቅ ብሎ ብዙ የአሳማ መንጋ ተሰማርቶ ነበር።+ 31 አጋንንቱም “የምታስወጣን ከሆነ ወደ አሳማው መንጋ ስደደን” ብለው ይማጸኑት ጀመር።+ 32 እሱም “ሂዱ!” አላቸው። እነሱም ወጥተው ወደ አሳማዎቹ ሄዱ፤ የአሳማውም መንጋ በሙሉ ከገደሉ አፋፍ እየተንደረደረ በመውረድ ባሕሩ ውስጥ ሰጥሞ አለቀ። 33 እረኞቹ ግን ሸሽተው ወደ ከተማው በመሄድ አጋንንት ባደሩባቸው ሰዎች ላይ የተፈጸመውን ጨምሮ የሆነውን ነገር ሁሉ አወሩ።