20 ሦስተኛው ቀን ደግሞ ፈርዖን የልደት በዓሉን የሚያከብርበት ዕለት ነበር፤+ እሱም ለአገልጋዮቹ በሙሉ ግብዣ አዘጋጀ። አገልጋዮቹ ባሉበትም የመጠጥ አሳላፊዎቹን አለቃና የዳቦ ጋጋሪዎቹን አለቃ ከእስር ቤት አስወጣቸው። 21 የመጠጥ አሳላፊዎቹንም አለቃ ወደ መጠጥ አሳላፊነት ሹመቱ መለሰው፤ እሱም እንደቀድሞው ለፈርዖን ጽዋውን ይሰጠው ጀመር። 22 የዳቦ ጋጋሪዎቹን አለቃ ግን ዮሴፍ ሕልማቸውን በፈታላቸው መሠረት ሰቀለው።+