-
ማቴዎስ 15:22-28አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
22 በዚያ ክልል የምትኖር አንዲት ፊንቄያዊት* ሴት መጥታ “ጌታ ሆይ፣ የዳዊት ልጅ፣ ምሕረት አድርግልኝ። ልጄን ጋኔን ስለያዛት ክፉኛ እየተሠቃየች ነው” ብላ ጮኸች።+ 23 እሱ ግን ምንም መልስ አልሰጣትም። ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ ቀርበው “ይህች ሴት ከኋላችን እየተከተለች ስለምትጮኽ እባክህ አሰናብታት” እያሉ ይለምኑት ጀመር። 24 እሱም መልሶ “እኔ የተላክሁት ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች እንጂ ለሌላ ለማንም አይደለም” አለ።+ 25 ሴትየዋ ግን ቀርባ “ጌታ ሆይ፣ እርዳኝ!” እያለች ሰገደችለት።* 26 እሱም መልሶ “የልጆችን ዳቦ ወስዶ ለቡችሎች መጣል ተገቢ አይደለም” አለ። 27 እሷም “አዎ ጌታ ሆይ፣ ግን እኮ ቡችሎችም ከጌቶቻቸው ማዕድ የሚወድቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ” አለች።+ 28 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ መልሶ “አንቺ ሴት፣ እምነትሽ ታላቅ ነው፤ በይ እንደ ፍላጎትሽ ይሁንልሽ” አላት። ልጇም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ተፈወሰች።
-