ኢሳይያስ 50:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ለሚገርፉኝ ጀርባዬን፣ጢም ለሚነጩም ጉንጮቼን ሰጠሁ። ፊቴን፣ ከሚያዋርዱ ነገሮችና ከትፋት አልሰወርኩም።+ ኢሳይያስ 53:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ሰዎች የናቁትና ያገለሉት፣+ሥቃይን ያየ፣* ሕመምንም የሚያውቅ ሰው ነበር። ፊቱ የተሰወረብን ያህል ነበር።* ሰዎች ናቁት፤ እኛም ከቁብ አልቆጠርነውም።+ ማቴዎስ 26:67, 68 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 67 ከዚያም ፊቱ ላይ ተፉበት፤+ በቡጢም መቱት።+ ሌሎቹም በጥፊ እየመቱት+ 68 “ክርስቶስ ሆይ፣ ነቢይ ከሆንክ እስቲ ማን እንደመታህ ንገረን?” አሉት።