-
ማርቆስ 3:14-19አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
14 ከዚያም 12 ሰዎች መርጦ ሐዋርያት ብሎ ሰየማቸው፤* እነዚህ አብረውት የሚሆኑ ከመሆኑም ሌላ ከጊዜ በኋላ ለስብከት ሥራ የሚልካቸውና 15 አጋንንትን የማስወጣት ሥልጣን የሚሰጣቸው ናቸው።+
16 የመረጣቸውም* 12 ሐዋርያት+ እነዚህ ናቸው፦ ጴጥሮስ ብሎ የሰየመው ስምዖን፣+ 17 የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብና የያዕቆብ ወንድም ዮሐንስ (እነዚህን ቦአኔርጌስ ብሎ የሰየማቸው ሲሆን ትርጉሙም “የነጎድጓድ ልጆች” ማለት ነው)፣+ 18 እንድርያስ፣ ፊልጶስ፣ በርቶሎሜዎስ፣ ማቴዎስ፣ ቶማስ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፣ ታዴዎስ፣ ቀነናዊው* ስምዖን 19 እንዲሁም በኋላ ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ።
ከዚያ በኋላ ወደ አንድ ቤት ሄደ፤
-