-
ማርቆስ 5:2-10አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
2 ኢየሱስ ከጀልባ እንደወረደ፣ ርኩስ መንፈስ ያደረበት አንድ ሰው ከመቃብር ቦታ ወጥቶ ከእሱ ጋር ተገናኘ። 3 ይህ ሰው በመቃብር ቦታ ይኖር የነበረ ሲሆን እስከዚያ ጊዜ ድረስ በሰንሰለት እንኳ አጥብቆ ሊያስረው የቻለ አንድም ሰው አልነበረም። 4 ብዙ ጊዜ በእግር ብረትና በሰንሰለት ይታሰር የነበረ ቢሆንም ሰንሰለቱን ይበጣጥስ፣ እግር ብረቱንም ይሰባብር ነበር፤ እሱን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የሚያስችል ጉልበት ያለው አንድም ሰው አልነበረም። 5 ዘወትር ሌሊትና ቀን በመቃብር ቦታና በተራሮች ላይ ይጮኽ እንዲሁም ሰውነቱን በድንጋይ ይተለትል ነበር። 6 ኢየሱስን ከሩቅ ባየው ጊዜ ግን ወደ እሱ ሮጦ በመሄድ ሰገደለት።+ 7 ከዚያም በታላቅ ድምፅ እየጮኸ “የልዑል አምላክ ልጅ ኢየሱስ ሆይ፣ እኔ ከአንተ ጋር ምን ጉዳይ አለኝ? እንዳታሠቃየኝ በአምላክ ስም አስምልሃለሁ” አለው።+ 8 ይህን ያለው ኢየሱስ “አንተ ርኩስ መንፈስ ከዚህ ሰው ውጣ”+ ብሎት ስለነበር ነው። 9 ኢየሱስም “ስምህ ማን ነው?” ብሎ ጠየቀው። እሱም “ብዙ ስለሆንን ስሜ ሌጌዎን* ነው” ብሎ መለሰለት። 10 መናፍስቱን ከአገሪቱ እንዳያስወጣቸውም ኢየሱስን ተማጸነው።+
-