ማርቆስ 12:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 ሁለተኛው ደግሞ ‘ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ’ የሚል ነው።+ ከእነዚህ የሚበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለም።” ዮሐንስ 13:34 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ እንደወደድኳችሁ+ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ።+ 1 ተሰሎንቄ 4:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ይሁን እንጂ እናንተ ራሳችሁ እርስ በርስ እንድትዋደዱ ከአምላክ ስለተማራችሁ+ የወንድማማች ፍቅርን በተመለከተ+ እንድንጽፍላችሁ አያስፈልግም። 1 ጴጥሮስ 4:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ከሁሉም በላይ አንዳችሁ ለሌላው የጠለቀ ፍቅር ይኑራችሁ፤+ ምክንያቱም ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናል።+