2 ሳሙኤል 7:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 አሁንም አገልጋዬን ዳዊትን እንዲህ በለው፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ እንድትሆን+ መንጋ ከምትጠብቅበት ስፍራ+ ወሰድኩህ። 2 ሳሙኤል 7:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 የሕይወት ዘመንህ አብቅቶ+ ከአባቶችህ ጋር በምታንቀላፋበት ጊዜ ከአንተ በኋላ ከአብራክህ የሚወጣውን ዘርህን አስነሳለሁ፤ መንግሥቱንም አጸናለሁ።+ ሉቃስ 1:32 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 እሱም ታላቅ ይሆናል፤+ የልዑሉም አምላክ ልጅ ይባላል፤+ ይሖዋ* አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤+ 2 ጢሞቴዎስ 2:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት እንደተነሳ+ እንዲሁም የዳዊት ዘር+ እንደሆነ አስታውስ፤ እኔም የምሰብከው ምሥራች ይህ ነው፤+
8 አሁንም አገልጋዬን ዳዊትን እንዲህ በለው፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ እንድትሆን+ መንጋ ከምትጠብቅበት ስፍራ+ ወሰድኩህ።