ዘፍጥረት 3:23, 24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 ይህን ካለ በኋላም የተገኘበትን መሬት እንዲያርስ፣+ ይሖዋ አምላክ አዳምን ከኤደን የአትክልት ስፍራ+ አባረረው። 24 ሰውየውንም አስወጣው፤ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ በኤደን የአትክልት ስፍራ በስተ ምሥራቅ በኩል ኪሩቤልና+ ያለማቋረጥ የሚሽከረከር የነበልባል ሰይፍ አስቀመጠ። ዘዳግም 17:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 እሱን ለመግደል መጀመሪያ እጃቸውን የሚያነሱት ምሥክሮቹ መሆን ይኖርባቸዋል፤ ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ እጁን ያንሳበት። ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ።+ ቲቶ 3:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ኑፋቄ+ የሚያስፋፋን ሰው ከአንዴም ሁለቴ አጥብቀህ ምከረው።*+ ካልሰማህ ግን ከእሱ ራቅ፤+ 2 ዮሐንስ 10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ማንም ሰው ወደ እናንተ ቢመጣና ይህን ትምህርት ይዞ ባይመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት+ ወይም ሰላም አትበሉት።
23 ይህን ካለ በኋላም የተገኘበትን መሬት እንዲያርስ፣+ ይሖዋ አምላክ አዳምን ከኤደን የአትክልት ስፍራ+ አባረረው። 24 ሰውየውንም አስወጣው፤ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ በኤደን የአትክልት ስፍራ በስተ ምሥራቅ በኩል ኪሩቤልና+ ያለማቋረጥ የሚሽከረከር የነበልባል ሰይፍ አስቀመጠ።