22 እናንተ ግን የቀረባችሁት ወደ ጽዮን ተራራና+ የሕያው አምላክ ከተማ ወደሆነችው ወደ ሰማያዊቱ ኢየሩሳሌም፣+ አንድ ላይ ወደተሰበሰቡ አእላፋት መላእክት፣ 23 በሰማያት ወደተመዘገበው የበኩራት ጉባኤ፣+ የሁሉ ፈራጅ ወደሆነው አምላክ፣+ ፍጽምና እንዲያገኙ ወደተደረጉት+ ጻድቃን መንፈሳዊ ሕይወት፣+ 24 የአዲስ ቃል ኪዳን+ መካከለኛ ወደሆነው ወደ ኢየሱስና+ ከአቤል ደም በተሻለ ሁኔታ ወደሚናገረው ወደተረጨው ደም ነው።+