16 ሆኖም ቅዱስ የሆነውን ነገር ከሚጻረሩ ከንቱ ንግግሮች ራቅ፤+ እንዲህ ያሉ ንግግሮች ሰዎች ይበልጥ ፈሪሃ አምላክ የሌላቸው እየሆኑ እንዲሄዱ ያደርጋሉና፤ 17 እንዲህ ያሉ ንግግሮችን የሚናገሩ ሰዎች ቃላቸው እንደተመረዘ ቁስል ይሰራጫል። ከእነሱም መካከል ሄሜኔዎስና ፊሊጦስ ይገኙበታል።+ 18 እነዚህ ሰዎች ‘ትንሣኤ ቀደም ብሎ ተከናውኗል’ ብለው በመናገር ከእውነት ርቀዋል፤+ ደግሞም የአንዳንዶችን እምነት እያፈረሱ ነው።