2 ተሰሎንቄ 2:1, 2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ይሁን እንጂ ወንድሞች፣ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መገኘትና+ ከእሱ ጋር ለመሆን አንድ ላይ መሰብሰባችንን+ በተመለከተ ይህን እንለምናችኋለን፤ 2 በመንፈስ በተነገረ ቃል* ወይም በቃል መልእክት ወይም ደግሞ ከእኛ የተላከ በሚመስል ደብዳቤ አማካኝነት የይሖዋ* ቀን+ ደርሷል ብላችሁ በማሰብ የማመዛዘን ችሎታችሁ በቀላሉ አይናወጥ፤+ ደግሞም አትደናገጡ። 2 ጢሞቴዎስ 4:3, 4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ትክክለኛውን ትምህርት* የማይታገሡበት ጊዜ ይመጣልና፤+ ከዚህ ይልቅ ከራሳቸው ፍላጎት ጋር በሚስማማ ሁኔታ ጆሯቸውን እንዲኮረኩሩላቸው* በዙሪያቸው አስተማሪዎችን ይሰበስባሉ።+ 4 እውነትን ከመስማት ጆሯቸውን ይመልሳሉ፤ ለተረትም ጆሮ ይሰጣሉ። 2 ጴጥሮስ 2:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ይሁን እንጂ በሕዝቡ መካከል ሐሰተኛ ነቢያት እንደነበሩ ሁሉ በእናንተም መካከል ሐሰተኛ አስተማሪዎች ይነሳሉ።+ እነዚህ ሰዎች ጥፋት የሚያስከትል ኑፋቄ በስውር ያስገባሉ፤ የዋጃቸውን+ ጌታ እንኳ ሳይቀር ክደው በራሳቸው ላይ ፈጣን ጥፋት ያመጣሉ።
2 ይሁን እንጂ ወንድሞች፣ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መገኘትና+ ከእሱ ጋር ለመሆን አንድ ላይ መሰብሰባችንን+ በተመለከተ ይህን እንለምናችኋለን፤ 2 በመንፈስ በተነገረ ቃል* ወይም በቃል መልእክት ወይም ደግሞ ከእኛ የተላከ በሚመስል ደብዳቤ አማካኝነት የይሖዋ* ቀን+ ደርሷል ብላችሁ በማሰብ የማመዛዘን ችሎታችሁ በቀላሉ አይናወጥ፤+ ደግሞም አትደናገጡ።
3 ትክክለኛውን ትምህርት* የማይታገሡበት ጊዜ ይመጣልና፤+ ከዚህ ይልቅ ከራሳቸው ፍላጎት ጋር በሚስማማ ሁኔታ ጆሯቸውን እንዲኮረኩሩላቸው* በዙሪያቸው አስተማሪዎችን ይሰበስባሉ።+ 4 እውነትን ከመስማት ጆሯቸውን ይመልሳሉ፤ ለተረትም ጆሮ ይሰጣሉ።
2 ይሁን እንጂ በሕዝቡ መካከል ሐሰተኛ ነቢያት እንደነበሩ ሁሉ በእናንተም መካከል ሐሰተኛ አስተማሪዎች ይነሳሉ።+ እነዚህ ሰዎች ጥፋት የሚያስከትል ኑፋቄ በስውር ያስገባሉ፤ የዋጃቸውን+ ጌታ እንኳ ሳይቀር ክደው በራሳቸው ላይ ፈጣን ጥፋት ያመጣሉ።