7 ከዚያም ሙሴ አሮንን እንዲህ አለው፦ “ወደ መሠዊያው ቀርበህ የኃጢአት መባህንና+ የሚቃጠል መባህን አቅርብ፤ ለራስህና ለቤትህም አስተሰርይ፤+ ይሖዋ ባዘዘውም መሠረት የሕዝቡን መባ አቅርብ፤+ እንዲሁም ለእነሱ አስተሰርይ።”+
8 አሮንም ወዲያው ወደ መሠዊያው ቀርቦ ስለ ራሱ የኃጢአት መባ ሆኖ የሚቀርበውን ጥጃ አረደ።+ 9 ከዚያም ወንዶች ልጆቹ ደሙን አቀረቡለት፤+ እሱም ጣቱን ደሙ ውስጥ በመንከር የመሠዊያውን ቀንዶች ቀባ፤ የቀረውንም ደም በመሠዊያው ሥር አፈሰሰው።+