ኢሳይያስ 65:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 እነሆ፣ አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር እየፈጠርኩ ነውና፤+የቀድሞዎቹ ነገሮች አይታሰቡም፤*ወደ ልብም አይገቡም።+ ኢሳይያስ 66:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 “እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር+ በፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ ሁሉ የእናንተም ዘርና ስማችሁ እንዲሁ ጸንቶ ይኖራል”+ ይላል ይሖዋ። ራእይ 21:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 እኔም አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር አየሁ፤+ የቀድሞው ሰማይና የቀድሞው ምድር አልፈዋልና፤+ ባሕሩም+ ከእንግዲህ ወዲህ የለም።