መዝሙር
የአሳፍ+ ማህሌት።
2 የአገልጋዮችህን ሬሳ ለሰማይ ወፎች፣
የታማኝ አገልጋዮችህንም ሥጋ ለምድር አራዊት ምግብ አድርገው ሰጥተዋል።+
3 ደማቸውን በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውኃ አፈሰሱ፤
እነሱንም የሚቀብር አንድም ሰው አልተረፈም።+
4 በጎረቤቶቻችን ዘንድ መሳለቂያ ሆንን፤+
በዙሪያችን ያሉትም ያፌዙብናል፤ ደግሞም ይዘብቱብናል።
5 ይሖዋ ሆይ፣ የምትቆጣው እስከ መቼ ነው? ለዘላለም?+
ቁጣህስ እንደ እሳት የሚነደው እስከ መቼ ነው?+
6 አንተን በማያውቁ ብሔራት፣
ስምህንም በማይጠሩ መንግሥታት ላይ ቁጣህን አፍስስ።+
7 ያዕቆብን በልተውታልና፤
የትውልድ አገሩንም አውድመዋል።+
8 አባቶቻችን በሠሩት ስህተት እኛን ተጠያቂ አታድርገን።+
ፈጥነህ ምሕረት አድርግልን፤+
በጭንቀት ተውጠናልና።
10 ብሔራት “አምላካቸው የት አለ?” ለምን ይበሉ?+
በፈሰሰው የአገልጋዮችህ ደም የተነሳ የሚወሰድባቸውን የበቀል እርምጃ፣
ዓይናችን እያየ ብሔራት ይወቁት።+
11 እስረኛው የሚያሰማውን ሲቃ ስማ።+