ኢሳይያስ
57 ጻድቁ ሞቷል፤
ይህን ግን ማንም ልብ አይልም።
2 እሱ ሰላም ያገኛል።
በቅንነት የሚሄዱ ሁሉ አልጋቸው* ላይ ያርፋሉ።
4 የምታሾፉት በማን ላይ ነው?
አፋችሁን የምትከፍቱትና ምላሳችሁን የምታወጡትስ በማን ላይ ነው?
እናንተ የዓመፅ ልጆች፣
5 በትላልቅ ዛፎች መካከል፣
ቅጠሉ በተንዠረገገም ዛፍ ሥር ሁሉ በስሜት የተቃጠላችሁ፣+
በሸለቆዎች* ውስጥ፣ በቋጥኞች መካከል
ልጆችን የምታርዱ አይደላችሁም?+
6 በሸለቆው* ውስጥ ያሉት ለስላሳ ድንጋዮች ድርሻዎችሽ ናቸው።+
አዎ፣ እነዚህ ዕጣ ፋንታዎችሽ ናቸው።
ለእነሱም ጭምር የመጠጥ መባ አፍስሰሻል፤ ስጦታም አቅርበሻል።+
ታዲያ እኔ በእነዚህ ነገሮች ደስ ልሰኝ ይገባል?*
8 ከበሩና ከመቃኑ ጀርባ የመታሰቢያ ምልክትሽን አደረግሽ።
እኔን ተውሽኝ፤ እርቃንሽንም ገለጥሽ፤
ወደ ላይ ወጣሽ፤ መኝታሽንም አሰፋሽ።
ከእነሱም ጋር ቃል ኪዳን ገባሽ።
መልእክተኞችሽን ወደ ሩቅ ቦታ ላክሽ፤
በመሆኑም ወደ መቃብር* ወረድሽ።
10 ብዛት ያላቸውን መንገዶችሽን በመከተል ደከምሽ፤
ሆኖም ‘ተስፋ የለውም!’ አላልሽም።
ጉልበትሽ ታደሰ።
ተስፋ ያልቆረጥሽው* ለዚህ ነው።
እኔን አላስታወስሽም።+
ልብ ያልሽውም ነገር የለም።+
እኔ ዝም አላልኩም? ደግሞስ ከመናገር አልተቆጠብኩም?*+
በመሆኑም እኔን አልፈራሽም።
14 እንዲህ ይባላል፦ ‘መንገድ ሥሩ! መንገድ ሥሩ! መንገዱን አዘጋጁ!+
ሕዝቤ ከሚሄድበት መንገድ ላይ ማንኛውንም እንቅፋት አስወግዱ።’”
“ከፍ ባለውና ቅዱስ በሆነው ስፍራ እኖራለሁ፤+
ደግሞም የተሰበረ ልብ ካለውና መንፈሱ ከተደቆሰው ጋር እሆናለሁ፤
ይህም የችግረኞችን መንፈስ አነሳሳ ዘንድ፣
የተሰበረ ልብ ያላቸውንም አነቃቃ ዘንድ ነው።+
እሱ ግን እንደ ከዳተኛ የልቡን መንገድ ተከትሎ መሄዱን ገፋበት።+
19 “የከንፈሮችን ፍሬ እፈጥራለሁ።
በሩቅም ሆነ በቅርብ ያለው ዘላቂ ሰላም ያገኛል፤+
እኔም እፈውሰዋለሁ” ይላል ይሖዋ።
20 “ክፉዎች ግን ጸጥ ማለት እንደማይችል የሚናወጥ ባሕር ናቸው፤
ውኃውም የባሕር ውስጥ ዕፀዋትንና ጭቃን ያወጣል።