መዝሙር
የዳዊት ማህሌት፤ ማስታወሻ ሆኖ የሚያገለግል።
38 ይሖዋ ሆይ፣ በቁጣህ አትውቀሰኝ፤
ተናደህም አታርመኝ።+
2 ፍላጻዎችህ እስከ ውስጥ ድረስ ወግተውኛልና፤
እጅህም ተጭኖኛል።+
ከኃጢአቴም የተነሳ አጥንቶቼ ሰላም የላቸውም።+
4 የፈጸምኳቸው ስህተቶች በራሴ ላይ ያንዣብባሉና፤+
እንደ ከባድ ሸክም በጣም ከብደውኛል።
5 ከሞኝነቴ የተነሳ
ቁስሌ ሸተተ፤ ደግሞም አመረቀዘ።
6 በጭንቀት ተዋጥኩ፤ አንገቴንም ደፋሁ፤
ቀኑን ሙሉ በሐዘን ተውጬ እመላለሳለሁ።
8 ደነዘዝኩ፤ ፈጽሞም ደቀቅኩ፤
በጭንቀት ከተዋጠው ልቤ የተነሳ እጅግ እቃትታለሁ።*
9 ይሖዋ ሆይ፣ ምኞቴ ሁሉ በፊትህ ነው፤
የማሰማው ሲቃም ከአንተ የተሰወረ አይደለም።
10 ልቤ በኃይል ይመታል፤ ጉልበቴ ከድቶኛል፤
የዓይኔም ብርሃን ጠፍቷል።+
11 ከቁስሌ የተነሳ ወዳጆቼና ጓደኞቼ ሸሹኝ፤
በቅርብ የሚያውቁኝ ሰዎችም ከእኔ ራቁ።
14 መስማት እንደማይችል፣
በአፉም የመከላከያ መልስ እንደማይሰጥ ሰው ሆንኩ።
16 “በእኔ ውድቀት አይፈንድቁ፤
ወይም እግሬ ቢንሸራተት በእኔ ላይ አይኩራሩ” ብያለሁና።
17 ልወድቅ ምንም አልቀረኝም ነበርና፤
ሥቃዬም ከእኔ አልተለየም።+
20 ላደረግኩት መልካም ነገር ክፉ መለሱልኝ፤
መልካም የሆነውን ነገር በመከተሌ ይቃወሙኝ ነበር።
21 ይሖዋ ሆይ፣ አትተወኝ።
አምላክ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ።+
22 አዳኜ ይሖዋ ሆይ፣
እኔን ለመርዳት ፍጠን።+