ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት ማህሌት።
20 በጭንቀት ቀን ይሖዋ ይስማህ።
የያዕቆብ አምላክ ስም ይጠብቅህ።+
2 ከቅዱሱ ስፍራ እርዳታ ይላክልህ፤+
ከጽዮንም ደግፎ ይያዝህ።+
3 በስጦታ የምታቀርበውን መባ ሁሉ ያስብልህ፤
የሚቃጠል መባህን በሞገስ ዓይን ይቀበልህ። (ሴላ)
4 የልብህን ፍላጎት ያሟላልህ፤+
ዕቅድህንም ሁሉ ያሳካልህ።
5 በማዳን ሥራህ በደስታ እልል እንላለን፤+
በአምላካችን ስም ዓርማችንን ወደ ላይ ከፍ እናደርጋለን።+
ይሖዋ የለመንከውን ሁሉ ይፈጽምልህ።
6 ይሖዋ የቀባውን እንደሚያድን አሁን አወቅኩ።+
በቀኝ እጁ በሚያከናውነው ታላቅ የማዳን ሥራ፣+
ቅዱስ ከሆኑት ሰማያቱ ይመልስለታል።
7 አንዳንዶች በሠረገሎች፣ ሌሎች ደግሞ በፈረሶች ይታመናሉ፤+
እኛ ግን የአምላካችንን የይሖዋን ስም እንጠራለን።+
8 እነሱ ተዝለፍልፈው ወድቀዋል፤
እኛ ግን ተነስተን ቀጥ ብለን ቆመናል።+
9 ይሖዋ ሆይ፣ ንጉሡን አድን!+
እርዳታ ለማግኘት በተጣራን ቀን ይመልስልናል።+