ሚክያስ
7 ወዮልኝ! የበጋ ፍሬ* ከተሰበሰበና
ወይን የሚሰበሰብበት ጊዜ አብቅቶ
ቃርሚያ ከተለቀመ በኋላ
የሚበላ የወይን ዘለላ እንደማያገኝ ሰው ሆኛለሁ፤
በጣም የምመኘውን፣* በመጀመሪያው ወቅት የሚደርሰውን በለስም አላገኘሁም።
ሁሉም ደም ለማፍሰስ ያደባሉ።+
እያንዳንዱም የገዛ ወንድሙን በመረብ ያጠምዳል።
3 እጆቻቸው መጥፎ ነገር በማድረግ የተካኑ ናቸው፤+
ገዢው የሆነ ነገር እንዲደረግለት ይጠይቃል፤
ፈራጁ ክፍያ ይጠይቃል፤+
ታዋቂ የሆነው ሰው የራሱን ፍላጎት ይገልጻል፤*+
እነሱም አንድ ላይ ሆነው ያሴራሉ።*
4 ከእነሱ መካከል የተሻለ የተባለው እንደ እሾህ ነው፤
እጅግ ቅን የተባለው ደግሞ ከእሾህ ቁጥቋጦ የከፋ ነው።
ጠባቂዎችህ የተናገሩለት፣ አንተ የምትጎበኝበት ቀን ይመጣል።+
እነሱ አሁን ይሸበራሉ።+
5 ባልንጀራህን አትመን፤
ወይም በቅርብ ወዳጅህ አትታመን።+
በእቅፍህ ለምትተኛው ስለምትናገረው ነገር ተጠንቀቅ።
አምላኬ ይሰማኛል።+
8 ጠላቴ ሆይ፣ በእኔ ላይ በደረሰው ነገር ሐሴት አታድርጊ።
ብወድቅም እንኳ እነሳለሁ፤
በጨለማ ውስጥ ብቀመጥም ይሖዋ ብርሃን ይሆንልኛል።
እሱ ወደ ብርሃን ያወጣኛል፤
እኔም የእሱን ጽድቅ አያለሁ።
10 “አምላክህ ይሖዋ የት አለ?”
ስትለኝ የነበረችው ጠላቴም ታያለች፤
ኀፍረትም ትከናነባለች።+
ዓይኖቼም ያዩአታል።
በዚያን ጊዜ በጎዳና ላይ እንዳለ ጭቃ የምትረገጥ ቦታ ትሆናለች።
11 የድንጋይ ቅጥሮችሽ የሚገነቡበት ቀን ይሆናል፤
በዚያ ቀን ድንበሩ ይሰፋል።*
12 በዚያ ቀን ከአሦርና ከግብፅ ከተሞች፣
ከግብፅ አንስቶ እስከ ወንዙ* ድረስ፣
ከባሕር እስከ ባሕር፣ ከተራራም እስከ ተራራ ድረስ ያሉ ሰዎች
ወደ አንቺ ይመጣሉ።+
13 ምድሪቱም ከነዋሪዎቿና ከሠሩት ነገር* የተነሳ
ባድማ ትሆናለች።
እንደ ድሮው ዘመን በባሳንና በጊልያድ ይሰማሩ።+
15 “ከግብፅ ምድር በወጣችሁበት ዘመን እንደነበረው
ድንቅ ሥራዎችን አሳያችኋለሁ።+
16 ብሔራትም ያያሉ፤ ታላቅ ኃይል ቢኖራቸውም ያፍራሉ።+
እጃቸውን በአፋቸው ላይ ይጭናሉ፤
ጆሯቸው ይደነቁራል።
17 እንደ እባብ አፈር ይልሳሉ፤+
በምድር ላይ እንደሚሳቡ እንስሳት እየተንቀጠቀጡ ከምሽጎቻቸው ይወጣሉ።
በፍርሃት ተውጠው ወደ አምላካችን ወደ ይሖዋ ይመጣሉ፤
አንተንም ይፈሩሃል።”+
እሱ ለዘላለም አይቆጣም፤
ታማኝ ፍቅር በማሳየት ደስ ይሰኛልና።+
19 ዳግመኛ ምሕረት ያሳየናል፤+ በደላችንን በቁጥጥሩ ሥር ያደርጋል።*
ኃጢአታቸውን ሁሉ ወደ ጥልቅ ባሕር ትጥላለህ።+