መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በሸሚኒት ቅኝት፣* በባለ አውታር መሣሪያዎች የሚታጀብ። የዳዊት ማህሌት።
6 ይሖዋ ሆይ፣ በቁጣህ አትውቀሰኝ፤
በታላቅ ቁጣህም አታርመኝ።+
2 ይሖዋ ሆይ፣ ዝያለሁና ሞገስ አሳየኝ።*
ይሖዋ ሆይ፣ አጥንቶቼ ተንቀጥቅጠዋልና ፈውሰኝ።+
8 እናንተ መጥፎ ምግባር ያላችሁ ሁሉ ከእኔ ራቁ፤
ይሖዋ የለቅሶዬን ድምፅ ይሰማልና።+
9 ይሖዋ ሞገስ እንዲያሳየኝ የማቀርበውን ልመና ይሰማል፤+
ይሖዋ ጸሎቴን ይቀበላል።
10 ጠላቶቼ በሙሉ ያፍራሉ፤ ደግሞም እጅግ ይደነግጣሉ፤
በድንገት ውርደት ተከናንበው ወደ ኋላ ያፈገፍጋሉ።+