ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በሸሚኒት ቅኝት። የዳዊት ማህሌት።
12 ይሖዋ ሆይ፣ አንድም ታማኝ ሰው ስለሌለ አድነኝ፤
ከሰው ልጆች መካከል ታማኞች ጠፍተዋል።
2 እርስ በርሳቸው ውሸት ይነጋገራሉ፤
በከንፈራቸው ይሸነግላሉ፤ አታላይ በሆነ ልብም ይናገራሉ።+
3 ይሖዋ የሚሸነግልን ከንፈር ሁሉ፣
ጉራ የሚነዛውንም ምላስ ይቆርጣል፤+
4 እነሱ “በምላሳችን እንረታለን።
አንደበታችንን እንዳሻን እንጠቀምበታለን፤
በእኛ ላይ ጌታ ሊሆን የሚችል ማን ነው?” ይላሉ።+
5 “የተጎሳቆሉት ሰዎች በመጨቆናቸው፣
ድሆችም በመቃተታቸው፣+
እርምጃ ለመውሰድ እነሳለሁ” ይላል ይሖዋ።
“በንቀት ዓይን ከሚመለከቷቸው ሁሉ እታደጋቸዋለሁ።”
6 የይሖዋ ቃል የጠራ ነው፤+
ከሸክላ በተሠራ ምድጃ እንደተጣራ ብር ሰባት ጊዜ የነጠረ ነው።
7 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ትጋርዳቸዋለህ፤+
እያንዳንዳቸውን ከዚህ ትውልድ ለዘላለም ትጠብቃቸዋለህ።
8 የሰው ልጆች ብልሹ ምግባርን ስለሚያስፋፉ፣
ክፉዎች እንዳሻቸው ይፈነጫሉ።+