መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በየዱቱን።* የአሳፍ+ መዝሙር። ማህሌት።
77 ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ አምላክ እጮኻለሁ፤
ወደ አምላክ እጮኻለሁ፤ እሱም ይሰማኛል።+
2 በጭንቀት በተዋጥኩ ቀን ይሖዋን እፈልጋለሁ።+
በሌሊት እጆቼ ያለምንም ፋታ ወደ እሱ እንደተዘረጉ ናቸው፤
ልጽናና አልቻልኩም።*
4 የዓይኔ ቆብ እንዳይከደን ያዝከው፤
በጣም ተረብሻለሁ፤ መናገርም አልችልም።
5 የድሮውን ጊዜ መለስ ብዬ አሰብኩ፤+
የጥንቶቹን ዓመታት አስታወስኩ።
7 ይሖዋ ለዘላለም ይጥለናል?+
ዳግመኛስ ሞገስ አያሳየንም?+
8 ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ተቋርጧል?
የተስፋ ቃሉስ ከትውልድ እስከ ትውልድ ከንቱ ሆኖ ይቀራል?
9 አምላክ ሞገሱን ማሳየት ረስቷል?+
ወይስ ቁጣው ምሕረት ከማሳየት እንዲቆጠብ አድርጎታል? (ሴላ)
ልዑሉ አምላክ ለእኛ ያለውን አመለካከት* ለውጧል” እያልኩ ልኖር ነው?
11 ያህ ያከናወናቸውን ሥራዎች አስታውሳለሁ፤
ጥንት የፈጸምካቸውን ድንቅ ተግባሮች አስታውሳለሁ።
13 አምላክ ሆይ፣ መንገዶችህ ቅዱስ ናቸው።
አምላክ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ታላቅ አምላክ ማን ነው?+
14 አንተ ድንቅ ነገሮችን የምታከናውን እውነተኛ አምላክ ነህ።+
ብርታትህን ለሕዝቦች ገልጠሃል።+
16 አምላክ ሆይ፣ ውኃዎቹ አዩህ፤
ውኃዎቹ ሲያዩህ ተረበሹ።+
ጥልቅ ውኃዎቹም ተናወጡ።
17 ደመናት ውኃ አዘነቡ።
በደመና የተሸፈኑት ሰማያት አንጎደጎዱ፤
ፍላጻዎችህም እዚህም እዚያም ተወነጨፉ።+