ኢሳይያስ
48 እናንተ ራሳችሁን በእስራኤል ስም የምትጠሩ፣+
ከይሁዳ ምንጭ የፈለቃችሁ፣*
በእውነትና በጽድቅ ባይሆንም
በይሖዋ ስም የምትምሉና+
የእስራኤልን አምላክ የምትጠሩ
የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ ይህን ስሙ።+
3 “ከብዙ ዘመን በፊት የቀድሞዎቹን* ነገሮች ነግሬአችኋለሁ።
ከአፌም ወጥተዋል፤
እንዲታወቁም አድርጌአለሁ።+
በድንገት እርምጃ ወሰድኩ፤ እነሱም ተፈጸሙ።+
6 አንተም ሰምተሃል፤ ደግሞም ይህን ሁሉ አይተሃል።
ከአሁን ጀምሮ አዳዲስ ነገሮችን፣
የማታውቃቸውን ጥብቅ ሚስጥሮች እነግርሃለሁ።+
10 እነሆ፣ እንደ ብር ባይሆንም አንጥሬሃለሁ።+
ክብሬን ለማንም አልሰጥም።*
12 ያዕቆብ ሆይ፣ የጠራሁህም እስራኤል ሆይ፣ ስማኝ።
እኔ ምንጊዜም ያው ነኝ።+ የመጀመሪያው እኔ ነኝ፤ የመጨረሻውም እኔ ነኝ።+
እነሱን ስጠራቸው በአንድነት ይቆማሉ።
14 ሁላችሁም አንድ ላይ ተሰብስባችሁ ስሙ።
ከመካከላቸው እነዚህን ነገሮች ያሳወቀ ማን ነው?
ይሖዋ ወዶታል።+
15 እኔ ራሴ ተናግሬአለሁ፤ እሱንም ጠርቼዋለሁ።+
አምጥቼዋለሁ፤ መንገዱም የተቃና ይሆናል።+
16 ወደ እኔ ቅረቡ፤ ደግሞም ይህን ስሙ።
ከመጀመሪያው አንስቶ በሚስጥር አልተናገርኩም።+
ከተፈጸመበት ጊዜ አንስቶ እኔ በዚያ ነበርኩ።”
አሁንም ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ መንፈሱም * ልኮኛል።
17 የሚቤዥህ፣ የእስራኤል ቅዱስ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦+
ስማቸው ከፊቴ አይጠፋም ወይም አይደመሰስም።”
ከከለዳውያን ሽሹ!
ይህን በእልልታ አስታውቁ! አውጁትም!+
እስከ ምድር ዳርቻ እንዲሰማ አድርጉ።+
እንዲህም በሉ፦ “ይሖዋ አገልጋዩን ያዕቆብን ተቤዥቶታል።+
21 ባድማ በሆኑ ቦታዎች በመራቸው ጊዜ አልተጠሙም።+
ከዓለት ውስጥ ውኃ አፈለቀላቸው፤
ዓለቱን ሰንጥቆ ውኃ አንዶለዶለላቸው።”+