መዝሙር
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ “በአበቦች” የሚዘመር። የዳዊት መዝሙር።
69 አምላክ ሆይ፣ ውኃ ሕይወቴን አደጋ ላይ ስለጣላት* አድነኝ።+
2 መቆሚያ ስፍራ በሌለበት ጥልቅ ማጥ ውስጥ ሰምጫለሁ።+
ጥልቅ ውኃዎች ውስጥ ገባሁ፤
ኃይለኛ ጅረትም ጠርጎ ወሰደኝ።+
3 ከመጮኼ ብዛት የተነሳ ደከምኩ፤+
ድምፄም ጎረነነ።
አምላኬን በመጠባበቅ ዓይኖቼ ፈዘዙ።+
ሊያጠፉኝ የሚፈልጉ፣
ተንኮለኛ የሆኑ ጠላቶቼ እጅግ በዝተዋል።
ያልሰረቅኩትን ነገር እንድመልስ ተገደድኩ።
5 አምላክ ሆይ፣ ሞኝነቴን ታውቃለህ፤
ጥፋቴም ከአንተ የተሰወረ አይደለም።
6 ሉዓላዊ ጌታ የሆንከው የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ሆይ፣
አንተን ተስፋ የሚያደርጉ በእኔ የተነሳ አይፈሩ።
የእስራኤል አምላክ ሆይ፣
አንተን የሚሹ በእኔ የተነሳ አይዋረዱ።
8 ለወንድሞቼ እንደ እንግዳ፣
ለእናቴ ልጆች እንደ ባዕድ አገር ሰው ሆንኩ።+
11 ማቅ በለበስኩ ጊዜ፣
መቀለጃ* አደረጉኝ።
12 በከተማዋ መግቢያ የሚቀመጡት የመወያያ ርዕስ አደረጉኝ፤
ሰካራሞችም ስለ እኔ ይዘፍናሉ።
13 ይሁንና ይሖዋ ሆይ፣ ጸሎቴ ተሰሚነት ሊያገኝ በሚችልበት ጊዜ
ወደ አንተ ይድረስ።+
አምላክ ሆይ፣ በታማኝ ፍቅርህ ብዛት፣
አስተማማኝ በሆነው የማዳን ሥራህም መልስልኝ።+
14 ከማጡ አውጣኝ፤
እንድሰምጥ አትፍቀድ።
ከሚጠሉኝ ሰዎችና
ከጥልቁ ውኃ ታደገኝ።+
16 ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህ ጥሩ ስለሆነ መልስልኝ።+
ጭንቅ ውስጥ ነኝና በፍጥነት መልስልኝ።+
18 ወደ እኔ ቀርበህ ታደገኝ፤*
ከጠላቶቼ የተነሳ ዋጀኝ።
19 የደረሰብኝን ነቀፋ፣ ኀፍረትና ውርደት ታውቃለህ።+
ጠላቶቼን በሙሉ ታያለህ።
20 የተሰነዘረብኝ ነቀፋ ልቤን ሰብሮታል፤ ቁስሉም የሚድን ዓይነት አይደለም።*
24 ቁጣህን አውርድባቸው፤
የሚነደው ቁጣህም ድንገት ይምጣባቸው።+
26 አንተ የመታኸውን አሳደዋልና፤
ደግሞም አንተ ያቆሰልካቸውን ሰዎች ሥቃይ ሁልጊዜ ያወራሉ።
27 በበደላቸው ላይ በደል ጨምርባቸው፤
ከአንተም ጽድቅ ምንም ድርሻ አይኑራቸው።
29 እኔ ግን በጭንቅና በሥቃይ ላይ ነኝ።+
አምላክ ሆይ፣ የማዳን ኃይልህ ይጠብቀኝ።
30 ለአምላክ ስም የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ፤
እሱንም በምስጋና ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።
31 ይህ ከበሬ ይበልጥ ይሖዋን ያስደስተዋል፤
ቀንድና ሰኮና ካለው ወይፈን ይበልጥ ደስ ያሰኘዋል።+
32 የዋሆች ይህን ያያሉ፤ ሐሴትም ያደርጋሉ።
እናንተ አምላክን የምትፈልጉ፣ ልባችሁ ይነቃቃ።
34 ሰማይና ምድር፣
ባሕርና በውስጡ የሚንቀሳቀሱ ሁሉ ያወድሱት።+